የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የትንሣኤን በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

የትንሳኤን በዓል ስናከብር ጧሪ ደጋፊ የሌላቸው አቅመ ደካሞች፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውንና የተቸገሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመጎብኘት፣ ፍቅርና ተስፋ በመስጠት፣ አብሮ በማሳለፍ እና አቅም በፈቀደ መጠን ካለን ላይ በማካፈል፣ በመደገፍና በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነታችንን በመወጣት እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ።በዓሉ የሰላም የፍቅር፣ የመረዳዳት እና የመተሳሰብ እንዲሆንም መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡

መልካም በዓል!

Please follow and like us: