1 ሺህ 181 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል

በሶስት ዙር በረራ በተከናወነ በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 181 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር ከተመለሱት 1 ሺህ 181 ዜጎች ውስጥ 1139 ወንዶች፣ 25 ሴቶች እና 17 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 6 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ17ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

Please follow and like us: