የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች የሴት ልጅ ግርዛትን፣ያለዕድሜ ጋብቻ፣ያልተፈለገ እርግዝና እና በፆታዊ ጥቃት ዙሪያ ለመከላከል ያላቸው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተገለፀ።

ይህ የተገለጸው ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የመጡ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች በሴት ልጅ ግርዛት፣ያለዕድሜ ጋብቻ፣ያልታቀደ እርግዝና እና ፆታዊ ጥቃት በሚመለከት በተቀናጀ መንገድ ለመስራት የምክክር መድረክ ተካሂዷል፡፡\

በምክክር መድረኩ የተገኙት በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስተር የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ እንደገለፁት በአገራችን ታዳጊ ሴቶችን ወደ ትምህርት ቤት በማስገባት ረገድ አስደናቂ እርምጃ ያሳየች መሆኑን ጠቅሰው ይህም በ2003 ዓ.ም አጠቃላይ የምዝገባ መጠን 51% የነበረ ሲሆን በ2016ዓ.ም ወደ 95% ማሳደግ መቻሉን ገልፀዋል ።ሚኒስትር ድኤታዋ እንደገለፁት ምንም እንኳ የምዝገባ መጠኑ ከፍተኛ ቢሆንም የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የማጠናቀቅ መጠን ዝቅተኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡በዚህም ታዳጊ ሴቶች ትምህርታቸውን በአግባቡ መከታተል እንዳይችሉ መሰናክል የሆኑባቸውን ችግሮች የሴት ልጅ ግርዛት፣ያለዕድሜ ጋብቻ፣ያልታቀደ እርግዝና እና ፆታዊ ጥቃት ለመቀነስ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዋል ። ሚኒስትር ድኤታዋ አክለውም በተለይም የተጠቀሱ ችግሮችን ለመከላከል የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ጠቅሰዋል ።

በመድረኩ የተገኙት ደ/ር አብዱላሂ ሳሊፍ በዩኔስኮ የአፍሪካ ተጠሪ፣ በዩናይትድ ኔሽን በኢትዮጵያ የኤች አይቪ ጉዳይ ዳይሬክተር፣ እና የFAWE-ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተሮች በተመሣሣይ እንደገለጹት የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ችግሮቹን ለመከላከል ያላቸውን ጉልህ ሚና እንደሚጫወቱ ከማመላከታቸውም በተጨማሪ ይህን ፕሮግራም ቀጣይነት ባለው መልኩ በማስቀጠል ችግሮቹ መቀነስ እንዲቻል በቅንጅት ለመስራት ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል፡፡ የምክክር መድረኩ ከዚህ በፊት በሰኔ ወር 2015ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዶ ከነበረው ፕሮግራም የቀጠለ ሲሆን ታዳጊ ሴቶች ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ የሚያደጉ መሰናክሎችን በሚመለከት በGAGE የጥናትና ምርምር ድርጅት /Gender And Adolescence:Global Evidence/ ጥናት ቀርቦ ውይይት መደረጉ ይታወሳል።

ክብርት አለሚቱና የተወካዬች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ክብር ዶር ታደለ ውይይቱን የመሩት እንደሆነ ተመሳሳይ ውይይት በየደረጃው በቅንጅት መሰራት እንዳለበት ተገልፃል።በውይይቱ ስለሴት ልጅ ግርዛት አስከፊነት፤ባህልና ሀይማኖት መቀላቀል ተግዳሮት እንደሆነ ከተቀናጀን ለውጥ ለማምጣት ፤ቃል ገብተን መሄድ አለብን ብለዋል በተጨማሪ የትምህርት ዘርፍ ፖሊሲና የሕግ ማዕቀፍ፣ የሴቶችን ትምህርት የማግኘት መብት ከማረጋገጥና ተጠቃሚነት አንጻር በሚል fawe ጥናቱ ቀርቦ በጥናቱ ላይ ውይይት እንደሚካሄድበትና በሚቀጥለው ጊዜ በሀይማኖት አባቶች የተከናወኑ ስራዎች ሪፖርት ቀርቦ በቀጣይ መካሄድ ያለባቸውን ስራዎች በመለየት የጋራ ስምምነት የሚደረስባቸው ይሆናል፡፡

Please follow and like us: