የተቋሙ ሰራተኞች የስትራይድ ኢትዮጵያ 2024 ኤክስፖ ጎበኙ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ላይ በመገኘት ጉብኝት እያካሄዱ ይገኛል።

የስትራይድ ኢትዮጵያ 2024 ኤክስፖ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በይፋ መከፈቱ ይታወቃል።ዓመታዊው ኤክስፖ “ሳይንስ በር ይከፍታል፥ ቴክኖሎጂ ያስተሳስራል፤ ፈጠራ ወደ ፊት ያራምዳል” በሚል መሪ ሃሳብ በሳይንስ ሙዚየም እስከ ግንቦት 18/2016 ዓ.ም ለህዝብ ዕይታ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ተገልጿል።ትኩረቱን ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራና ዲጂታላይዜሽን ላይ ያደረገው ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖ በርካታ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ተቋማትን በማሳተፍ ላይ እንደሚገኝ በጉብኝቱ ወቅት መገንዘብ ተችሏል፡፡በኤክስፖ የተሳተፉ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖ የቀረቡ ስራዎች ኢትዮጵያ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ትልቅ የለውጥ እርምጃ ላይ እንደሆና ለዘርፉ ተጨማሪ አቅምና እውቀት እንደሚፈጥርም ገልጸዋል፡፡

Please follow and like us: