230 ኢትዮጵያውያን ከኦማን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

በኦማን ማቆያ ጣቢያዎች የሚገኙ ኢትዮጵያውንን ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ስራ 230 ዜጎች ተመልሰዋል።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር የተመለሱት 230 ዜጎች ሁሉም ወንዶች መሆናቸው ታውቋል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከሚያዚያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ከኦማን ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 1ሺህ 150 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል ። በኦማን የሚገኙ 1ሺህ 590 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር ለመመለስ መታቀዱ የሚታስ ነው።

Please follow and like us: