229 ኢትዮጵያውያን ከኦማን ወደ ሀገራቸው ተመልሱ

በኦማን ማቆያ ጣቢያዎች የሚገኙ ኢትዮጵያውንን ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ስራ 229 ዜጎች ተመልሰዋል።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር የተመለሱት 229 ዜጎች ሁሉም ወንዶች መሆናቸው ታውቋል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከሚያዚያ 29 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ከኦማን ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 1ሺህ 379 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል ። የኢፌዴሪ መንግስት እየሰራ ባለው ዜጋ ተኮር የዲፕሎማሲ ስራ በኦማን የሚገኙ 1ሺህ 590 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር ለመመለስ መታቀዱ የሚታስ ነው።

 

Please follow and like us: