1 ሺህ 183 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሱ

በሶስት ዙር በረራ በተከናወነ በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 183 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር የተመለሱት 1 ሺህ 183 ዜጎች ውስጥ 1ሺህ 151 ወንዶች፣ 66 ሴቶች እና 66 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 9 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

 

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ29ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

Please follow and like us: