1 ሺህ 103 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሱ

በሶስት ዙር በረራ በተከናወነ በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 103 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር የተመለሱት 1 ሺህ 103
ዜጎች ውስጥ 1087 ወንዶች፣ 8 ሴቶች እና 8 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 8 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ30ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

 

Please follow and like us: