እስካሁን ከ35ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ከሳውዲ አረቢያ መመለስ ተችሏል

የኢፌዴሪ መንግስት እየሰራ ባለው ዜጋ ተኮር ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራ እስካሁን ከ35ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ከሳውዲ አረቢያ በሰላም መመለስ ተችሏል።

በዛሬው ዕለት ብቻም በሶስት ዙር በረራ በተከናወነ ዜጎችን የመመለስ ስራ በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 132 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል። ተመላሾች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ 4 ታዳጊ ህጻናት ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡በአጠቃላይ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ35ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

 

Please follow and like us: