የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በልደታ የሚገኘውን በወንጀል ነክ ጉዳዮች ውስጥ ገብተው የተገኙ ህፃናት/ወጣቶች  ማቆያና የተሃድሶ ማዕከልን በዛሬው ዕለት ጎበኝተዋል።

ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የማዕከሉን የስራ እንቅሰቃሴ ተመልክተዋል፤ ታራሚዎችን ተዟዙረው ጎብኝተዋል። የማዕከሉ የስራ ኃላፊዎችንም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ አነጋግረዋል።

በጉብኝቱ ጊዜ፥ ማዕከሉ ከሻማዳ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን በተሃድሶ ማዕከሉ ያሉ የመሠረተ ልማት ክፍተቶችን ለመሙላት እያደረጉት ያለውን ጥረት አድንቀዋል። በዕለቱ ድርጅቱ ያስገነባውን ዘመናዊ የህጻናት መመገቢያ አዳራሽ እና ደረጃውን የጠበቀ የምግብ ማብሰያ ከነቁሳቁስ ጋር አስረክቧል፡፡

ሻማዳ ኢትዮጵያ እያደረገ ላለው የበጎ አድራጎት ስራ ክብርት ሚኒስትር ምስጋና አቅርበዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተለያዩ ባለድርሻና አጋር አካላትን በማስተባበር የተሃድሶ ማዕከሉን አገልግሎት አሠጣጥ ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራትን በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።

 

 

Please follow and like us: