1 ሺህ 188 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 188 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

የዛሬ ተመላሾች 1152 ወንዶች፣ 20 ሴቶችና 16 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ከእነዚህም መካከል እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ 20 ታዳጊ ህጻናት ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተደረገ ባለው ጥረት እስካሁን ከ37ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

 

Please follow and like us: