966 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 966 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

በዛሬው እለት በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ 641 ወንዶች፣ 321 ሴቶችና 4 ጨቅላ ህፃናት ወደ ሀገር የተመለሱ ሲሆኑ ከእነዚህም መካከል እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ 60 ታዳጊ ህጻናት ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል::

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተደረገው ጥረት እስካሁን ከ38 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

Please follow and like us: