875 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 875 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

በዛሬው እለት በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ ወደ ሀገር የተመለሱት 875 ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ከእነዚህም ወስጥ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ 18 ታዳጊ ህጻናት ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ እስካሁን ከ39ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

 

Please follow and like us: