የልማት ፕሮጀክቶች ጉብኝት – በሐረሪ ክልል!!

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በሐረሪ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀከቶችን ጎብኝተዋል።

የሥራ ኃላፊዎቹ በክልሉ የአስፋልት መንገድ እና ከ”መደመር” መጽሐፍ ሽያጭ በተገኘ ገቢ የሚገነባውን ኢኮ ፓርክ ግንባታን ተመልክተዋል። የጀጎል ዓለም አቀፍ ቅርስ ጥበቃ እና እንክብካቤ ስራዎችን እንዲሁም በውስጡ የሚገኙ ሙዚዬሞችን እና መስህቦችንም ጎብኝተዋል።

ሐረርን አረንጓዴና ጽዱ እንዲሁም ለነዋሪዎቿ የተመቸችና ቱሪስቶችን የምትስብ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች መከናወናቸውም ተገልጿል። በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት መገለጹን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

 

Please follow and like us: