1 ሺህ 167 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሱ

በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 167 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

በዛሬው እለት በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ ወደ ሀገር የተመለሱት 1 ሺህ 167 ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ 16 ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ዜጎችን ወደ ሀገር ለመመለስ እየተከናወነ በሚገኘው ስራ እስካሁን ከ40ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

 

Please follow and like us: