በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ በኢትዮጵያ የሴቶች ሰላምና ደህንነት  ለብሔራዊ የድርጊት መርሃ ግብር ዝግጅት ግብአት ማሰባሰቢያ  የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተመራ ብሔራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ  የሴቶች ሰላምና ደህንነት ላይ ለብሔራዊ የድርጊት መርሃ ግብር ዝግጅት ግብአት ማሰባሰቢያ  የምክክር መድረክ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ በማካሄድ ላይ ነው።

ብሔራዊ የድርጊት መርሃ ግብሩ ቀደም ሲል በድሬዳዋ ከተማ መስተዳደር፣ በሀረሪና የአፋር ክልልን ጨምሮ በፌደራል ደረጃ የሚገኙ  የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች፤ ውስጥ ለሚገኙ 432 ለሚሆኑ ከተለያዪ አደረጃጀት ለተመረጡ ባለድርሻ አካላት በመሰጠት ላይ መሆኑን በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአካቶ ትግበራ ማብቃት ዴስክ ኃላፊ  አቶ ጌቱ በላይ ባቀረቡት ፅሁፍ ላይ ገልፀዋል ። ብሔራዊ የድርጊት መርሃ ግብሩ በሴቶች፣ የሰላም እና የጸጥታ አጀንዳዎች ላይ የሚወሰደውን እርምጃ አካባቢያዊ ለማድረግ የመንግስትን አካሄድ እና አቀራረብ የሚገልጽ በብሔራዊ ደረጃ የሚዘጋጅ የስትራቴጂ ሰነድ ነው።

ሰነዱ በግጭት ሁኔታዎች ውስጥ የሴቶች እና ልጃገረዶች ሰብአዊ መብቶችን ለማስጠበቅ በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገራት የሚወስዷቸውን ዓላማዎች እና ተግባራት ይዘረዝራል። በተጨማሪም በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ  የትጥቅ ግጭቶችን እና ጥቃቶችን በመከላከል እና ሴቶች በሰላም እና ደህንነት ላይ ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዲኖራቸው ሚናቸውን የሚያረጋግጥ የሚያረጋግጥ ሰነድ ነው፡፡

የዕለቱ የክብር እንግዳ የትግራይ ክልል የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ፍረወይኒ ገ/እግዚአብሔር እንደገለፁት በሴቶች ሰላም እና ደኅንነት ላይ በኢትዮጵያ  ብሎም በክልሉ የተሳካ ብሔራዊ የድርጊት መርሃ ግብር ለማዘጋጀት ከተለያየ ማህረሰብ ክፍል የመጡ ሰዎችን ሃሳቦችና አስተያየቶች በመስጠትና በመውሰድ በሴቶች ሰላምና ደህንነት ላይ ጠንካራ ብሔራዊ የድርጊት መርሃ ግብር ማዘጋጀት እንዲቻል ሁሉም የበኩሉን አስተዋፅዖ እንዲያበረክት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ። ብሔራዊ የድርጊት መርሃ ግብሩን ለማርቀቅና ለማጠናቀቅ የአውድ ዳሰሳ፣ ተቋማዊ ኦዲት፣ የህግ ማዕቀፍ ግምገማ ጥናቶችም መደረጋቸውተጠቅሷል ። ብሔራዊ የድርጊት መርሃ ግብሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሴቶች ሰላምና ደህንነት ላይ  ባወጣው ወሳኔ 1325 መሠረት ተግባራዊ የሚደረግ ነው።

የብሔራዊ የድርጊት መርሃ ግብሩን ተግባራዊ ለማድረግ ብሔራዊ የቴክኒክ ኮሚቴው  የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴርበዋናነት የሚያስፈፅም ሲሆን በአጋርነት የተለያዮ ሚኒስቴር መስሪያቤቶች ፣ ፌደራል ፖሊስ ፣የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ የተባበሩት መንግስታት ሴቶች፣ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም፣ የበይነ መንግስታት የልማት ባለስልጣን በዋናነት ይገኙበታል ።

 

Please follow and like us: