1 ሺህ 181 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 181 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ::

በዛሬው እለት በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ ወደ ሀገር የተመለሱት 1 ሺህ 181 ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ 16 ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 41ሺህ 700 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል

Please follow and like us: