“ሰው ሀገሩን ምን ያህል ይወዳል? ሲባል መልሱ “በበጎ ፈቃድ የሚያገለግላትን ያህል” ነው። – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ “በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደውን የ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ንቅናቄን ዛሬ አስጀምረዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ-ግብር ብቻ ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያ ባለ በብዝሃነት የደመቀ ሀገር ውስጥ ለጋራ ዕድገት እና የብልጽግና ግባችን መሳካት ወሳኝ መሳሪያ ነው ብለዋል። ይህ አገልግሎት ዜጎች ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ዕውቀታቸውንና ክህሎታቸውን ለሀገራቸው ዕድገት ያላቸውን ትብብርና ትጋት የሚያንጸባርቁበት ተግባር ነው ሲሉም ተናግረዋል።

በመሆኑም በዘንድሮ የክረምት ወራትም አገልግሎቱ ከታጠረበት የክረምት ወቅት በዘለለ የሁልጊዜ ተግባር ሆኖ የሚቀጥልበትን ስልት በመንደፍ፤ ታዳጊዎችና ወጣቶች ወደፊት የሚረከቧትን ብቻ ሳይሆን አሁን የሚኖሩባትንም ሀገር የሚገነቧት ራሳቸው መሆናቸውን በተግባር የሚያሳዩበት እንዲሆን ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

 

Please follow and like us: