1 ሺህ 93 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 93 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

በዛሬው እለት በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ ወደ ሀገር የተመለሱት 1 ሺህ 93 ዜጎች ውስጥ 1087 ወንዶች፣ 6 ሴቶች ሲሆኑ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ 14 ታዳጊዎችም ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ47ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

 

Please follow and like us: