954 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

በሶስት ዙር በረራ በተከናወነ በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ 954 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር ከተመለሱት 954 ዜጎች ውስጥ 747 ወንዶች፣ 198 ሴቶች፣ 9 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ 33 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ48,000 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

 

Please follow and like us: