5 ሚሊዮን ወላጆቻቸውን ያጡና ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ህጻናትን በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመደገፍ የሚያስችል ስራ ለመስራት የተቋቋመው ስትሪንግ ኮሚቴ የስራ ግምገማ አካሄደ

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በአሊያንስ ኬር ናው/Alliance Care Now (ANC) የበጎ አድራጎት ድርጅት እና ሌሎች የፌዴራል ተቋማት የተቋቋመ የሶስትዮሽ ጥምረት በቀጣዮቹ 5ዓመታት 5 ሚሊዮን ወላጆቻቸውን ያጡና ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ህጻናትን በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመደገፍ የሚያስችል ግብ በማስቀመጥ ወደ ተግባር ገብቷል።

በዛሬው ዕለትም ስትሪንግ ኮሚቴ በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን አስመልክቶ የስራ ግምገማውን አካሄዷል። በመድረኩ የኮሚቴ አባላት የአፈጻጸም ሪፓርት ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ረቂቅ የበጀት ፍላጎትን የሚያሳይ ኘሮፓዛል ቀርቦ ግብዓት ተሰጥቶበታል። እንዲሁም በቀረበው የፈንድ ፍላጎት ፕሮፖዛል ላይ በሰፊው በመወያየት ከእያንዳንዱ ተቋም የሚፈለግ ግዴታ የመለየት ስራም ተሰርቷል።

ብሄራዊ የፕሮግራም ማስጀመሪያ የጊዜ ሰሌዳ እና በሌሎችም በቀጣይ ሊሰሩ በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ኮሚቴው በሰፊው መክሯል፣ የቀጣይ የአቅጣጫም አስቀምጧል። በዚህም በጎ አድራጎት ድርጅቱን ጨምሮ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በቀጣይ ለስራው የሚያስፈልገውን ሀብት በማሰባሰብ፣ በየተቋማቱ የቴክኒክ ኮሚቴ በማቋቋም፣ የታቀዱ ስራዎች በተቀመጠላቸው የጊዜ ሠሌዳ መሰረት ተፈጻሚ እንዲሆኑ በቁርጠኛነት እንዲረባረቡና ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርጉ በመወያየት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

 

Please follow and like us: