በሀገር አቀፍ ደረጃ ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከልና ምላሽ በመስጠት ላይ ያሉ ተሞክሮዎች ላይ ያተኮረ የልምድ ልውውጥ መድረክ ተካሄደ።

በመድረኩ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች መብት ጥበቃና ምላሽ ስራ አስፈፃሚ አቶ ስለሺ ታደሰ እንደገለፁት

መድረኩ በዋናነት የቅንጅት ስራ ለማጠናከር መልካም ተሞክሮዎችን ለማጠናከር በተለይም የመከላከልና ምላሽ ለመስጠት በግጭትና በሰብአዊ ምላሽ እንዲሁም በመደበኛ የልማት ስራዎች አውድ ውስጥ እንዴት እየተተገበረ እንደሆነ ለመመልከት ታሳቢ ተደርጎ እንደተዘጋጀ ገልፀዋል ። በፍትህ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃናት ባለብዙ ዘርፍ ዳይሬክተር ወ/ሮ ዳግማዊት ትርፌ ፆታዊ ጥቃት ከመከላከልና ምላሽ መስጠት የተዘጋጀ ስትራቴጂክ ሰነድ አቅርበዋል።

ወ/ሮ ዳግማዊት እንደገለፁት ሁሉም በሚሰሩት ስራ ውስጥ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን ማካተታቸውን፣ አስፈላጊ ስልጠና መውሰዳቸውን፣ እንዲሁም ፕሮግራሞቻቸው ሥርዓተ ጾታ ተኮር፣ ትብብራዊና አሳታፊ መሆናቸውን ለማረጋገጥ፣ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት መከላከል፣ ተጋላጭነት መቀነስና የተሳትፎ የሚያደርጉ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል ።

በመድረኩ ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን በመከላከልና ምላሽ በመስጠት የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎችን እንዲሁም ግጭቶች ባሉባቸው ቦታዎች ሊከናወኑ የሚገባቸው ተግባራትን በማስተባበር የተቋማትን(GBV-OR)አወቃቀር እንዲሁም በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች መከላከልና ምላሽ መስጠትን አላማን ለማረጋገጥ የመስጠትና በተቋቋመው ብሄራዊ አስተባባሪ አካል እየተተገበሩ ያሉ ስራዎች ከተቋቋሙበት አላማና ግብ አንጻር የተሞክሮ ልውውጥና የቡድን ውይይቶች ተካሄደዋል።

በተጨማሪም የቅንጅት አወቃቀሮች ተሞክሮ የቀረበበትና እንዲሁም  ሁሉን አቀፍ የሆነ ደረጃውን የጠበቀ የአሰራር ስርአት SOP በወ/ሮ ህሊና ላቀው የሴቶች መብት ምላሽ ዴስክ ኃላፊ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። በመድረኩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ በሰብአዊ ምላሽና በመደበኛ የልማት ስራዎች አውድ ላይ ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን መከላከልና ምላሽ በመስጠት ላይ እየሰሩ ያሉ ተቋማት ተሳትፈውበታል።

 

Please follow and like us: