1 ሺህ 195 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል

በሳዐዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 195 ኢትዮጵያውያን በዛሬው እለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ ወደ ሀገር የተመለሱት 1ሺህ 104 ወንዶች፣ 76 ሴቶች፣ 15 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ከነዚህም ወስጥ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ 43 ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ዜጎችን ወደ ሀገር ለመመለስ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተሰራው ስራ እስካሁን ከ54 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

Please follow and like us: