የ2016 ዓ.ም ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስምሪት – በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ

(ሐዋሳ፣ ሰኔ 29/ 2016 ዓ.ም) በኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተባባሪነት “በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል ለ3ኛ ጊዜ እየተካሄደ ያለው የ2016 ዓ.ም ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ ተጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሀ – ግብሩ የክልሉ የሴቶች፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እመቤት ኢሳያስ፣ ምክትል የቢሮ ኃላፊና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደስታ ለገሰ እንዲሁም የሀዋሳ ከተማ አ/ር የሴቶች፣ የወጣቶችና ማህበራዊ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ፍሬህይወት ወ/ጻድቅ እና የመምሪያው ም/ኃላፊና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀደራ ሃርቃ በተገኙበት በጎ ፈቃደኛ ወጣቶቹ የደም ልገሳ እና የአካባቢ ጽዳት አከናውነዋል።

በጎ ፈቃደኛ ወጣቶቹ የተጀመሩ ስራዎችን ለማስቀጠል የተዘጋጀውን አርማ እና ባንዲራም ለክልሉ የስራ ኃላፊዎች አስረክበዋል።

 

Please follow and like us: