ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ገብተዋል

(ሆሳዕና፣ ሰኔ 29/ 2016 ዓ.ም) ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ማምሻውን ገብተዋል።

ወጣቶቹ ሆሳዕና ከተማ ሲደርሱ በክልሉና በከተማው የስራ ኃላፊዎች ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በዚሁ ወቅትም የከተማው ከንቲባ አቶ ዳዊት ጡሚዳዶ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘሪሁን እሸቱ የሰላምና የመቻቻል ከተማ ወደ ሆነች ሆሳዕና ከተማ እንኳን ደህና መጣችሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Please follow and like us: