1 ሺህ 174 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 174 ኢትዮጵያውያን በዛሬው እለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ዛሬ በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ ወደ ሀገር የተመለሱት 1 ሺህ 095 ወንዶች እና 79 ሴቶች ሲሆኑ ከነዚህም መካከል እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ 21 ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ እስካሁን ከ58 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

 

Please follow and like us: