ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በጋምቤላ ክልል ቆይታቸው የአካባቢ ጽዳት፣ የደም ልገሳና የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን አከናውነዋል።

ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ጋምቤላ ክልል ገብተዋል፤ በተለያዩ የስምሪት መስኮችም አገልግሎት ሰጥተዋል።

ወጣቶቹ ጋምቤላ ከተማ ሲገቡ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ቴንኳይ ጆክ፣ የተከበሩ ወ/ሮ አለሚቱ አለባቸው የክልሉ ምክር ቤት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ፣ ወ/ሮ ክሪምስ ሌሮ የክልሉ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ኮንግ ሬት የወጣቶች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ አኳይ ኡጁሉ የጋምቤላ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና ሌሎችም የክልሉ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገዋል።

ወጣቶቹ በጋምቤላ ክልል በነበራቸው ቆይታ የአካባቢ ጽዳትና የደም ልገሳ አከናውነዋል። በተጨማሪም ለከተማው ወጣቶች በሰላምና ህብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ሱሰኝነትን መከላከል እና ስብዕና ግንባታ ላይ ያተኮረ የንቅናቄ ስራ ሰርተዋል። በስርዓተ ጾታ እኩልነት፣ በጾታዊ ጥቃት፣ በስነተዋልዶ ጤና፣ በኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል ዙሪያም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናም ሰጥተዋል።

የዘንድሮው ወሰን ተሻጋሪ የክረምት ወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት “በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ሀሳብ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስተባባሪነት ለ3ኛ ጊዜ በ14ት የስምሪት መስኮች በመላ ሀገሪቱ እየተካሄደ ይገኛል።

 

Please follow and like us: