በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በኮምቦልቻ ከተማ ቆይታቸው የአካባቢ ጽዳትና ችግኝ ተከላ ተግባራትን አከናውነዋል

ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በአማራ ክልል ኮምቦልቻ ከተማ በመገኘት የአካባቢ ጽዳት እና ችግኝ ተከላ አገልግሎት ሰጥተዋል።

 

ወጣቶቹ ኮምቦልቻ ከተማ ሲገቡ የከተማው የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ጀማል መሃመድ፣ የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ አንሻ ሰይድ እና የወጣቶቸና ስፖርት መምሪያ ሃላፊ አቶ አስቻለው ብርሃኑ አቀባበል አደርገውላቸዋል። በተጨማሪም የከተማው ምክትል ከንቲባ አቶ ወንደሰን ልሳነወርቅ፣ የአብክመ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ሃላፊ አቶ ተሾመ ፈንታው እንዲሁም ሌሎች የከተማው የስራ ኃላፊዎች መርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው አነቃቂ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዚሁ ጊዜም ወጣቶች ለሰላም ዘብ ሊቆሙ እንደሚገባ እንዲሁም አንድነታቸውን በማጠናከር እና የጀመሩትን የበጎ ፈቃድ ተግባር በማስቀጥል ለአካባቢያቸውና ለሀገራቸው ሁለንተናዊ ዕድገት የበከላቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተገልጿል።

Please follow and like us: