የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በመሬት መንሸራተት አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ይገልጻል

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ ትናንት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት በሰው ሕይወት ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ይገልጻል፡፡

በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው የተጎጂ ቤተሰቦች እና ዘመድ ወዳጆች መፅናናትን ይመኛል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የበኩሉን እንደሚወጣም ይገልጻል፡፡

Please follow and like us: