ኢትዮጵያ በብሪክስ የወጣቶች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ትገኛለች

(አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17/ 2016 ዓ.ም) የኢትዮጵያ በብሪክስ የወጣቶች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ትገኛለች።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የተከበሩ ወጣት ፉአድ ገና በብሪክስ የወጣቶች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ወጣቶችን በመወከል እየተሳተፉ ይገኛሉ።ምክር ቤቱ በትምህርት፣ በስልጠናና አቅም ግንባታ፣ በስራፈጠራ፣ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን፣ በወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት፣

በጤናና በስፖርት ዘርፍ በብሪክስ አባል አገራት መካከል ሊኖር ስለሚገባው የትብብር ማዕቀፍ ዙሪያ በጥልቀት እየመከረ ይገኛል። ስብሰባው በራሺያ ኡሊያኖስከ ከተማ ከሐምሌ 15 እስከ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

Please follow and like us: