በክልሎች /ከተማ አስተዳደሮች የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፎረም ለማቋቋም የሚያስችል የውይይት ተካሄደ።

በክልሎች /ከተማ አስተዳደሮች የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፎረም ለማቋቋም የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሄደ። በመድረኩ የሴቶችና ማህባራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ሙና አህመድ የፎረሙ መመስረት ፣ ስራን በመስራት ደረጃ የሚታዩትን ክፍተቶች ይቀርፋል።

በተጨማሪም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳን ለመለካትና ለማዘመን ያስችላልም ብለዋል። ሚኒስትሯ እንደገለፁት በብሔራዊ የወጣቶች ፖሊሲ መነሻነት በ2002 ዓ.ም የተቀረፀው የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድን መሰረት በማድረግ ባለፉት 15 ዓመታት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተና በወጣቶች ብሎም በማኀበረሰቡ ዘንድ እየተለመደ የመጣ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል። በተሳታፊ ወጣቶች ቁጥር፣ ተጠቃሚ በሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲሁም አገልግሎቱ በገንዘብ ሲተመን ያለው አፈጻጸም በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉንም ጠቅሰዋል ። ለአብነትም 3ኛው ዙር ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለኢኮኖሚው ካበረከተው አስተዋጽኦ በተጨማሪ ትሩፋቶች ወጣቶቹ እንደ ሀገር ያለባቸውን ሀላፊነት የተገነዘቡበት ነው። ሚንስትር ድኤታዋ አክለውም የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቅንጅት የሚጠይቅ ሲሆን ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ከዩዝ ኔቶርክ ፎር ስስቴኔብል ዴቨሎፕምነት ባቀረበው የፕሮግራም ሰነድ መስረት Community Service As A pathway to Work programme አጠቃላይ አላማ ከሆኑት መካከል ወጣቶች ማህበረስባዊ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ላይ እንዲሳተፍ እድሎችን በመፍጠር እና የስራ ዝግጁነት ክህሎቶቻቸውን በማሳደግ ወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በጋራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

አቶ ኢሳይያስ አለማየሁ የዩዝ ኔትወርክ ፎር ሰስቴኔብል ድቭሎፕመንት ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው ወጣቶች በአካባቢያቸው በተለያዩ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ላይ በመሳተፍ መሰረታዊ የስራ ዝግጁነት ክህሎት እንዲያዳብሩ ለማስቻል የተነደፈ የአምስት አመት መርሀ ግብር ተግባራዊ መደረጉን ገልፀዋል ። አክለውም ዩዝ ኔትወርክ ፎር ሰስቴኔብል ድቭሎፕመንት ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በ5 ክልልሎች ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል ። የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፎረም በተመሳሳይ በዞን፣ በክፍለ ከተማ እና በወረዳ ደረጃ የክልሉን /የከተማ አስተዳደሩን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፎረሞች የሚቋቋሙ ይሆናል፡፡

Please follow and like us: