እንኳን ደስ አልዎት!!! ክብርት ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ የጋምቤላ ክልል የመጀመሪያዋ ሴት ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ ክብርት ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ የጋምቤላ ክልል የመጀመሪያዋ ሴት ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሹመዋል።

በመሆኑም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች የተሰማቸውን ደስታ እየገለጹ መጪው የስራ ዘመን የስኬት እንዲሆን በመመኘት የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላልፈዋል። ክብርት ወይዘሮ ዓለሚቱ ኡሞድ ቀደም ሲል የክልሉ ምክትል አፈ- ጉባኤ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

Please follow and like us: