1 ሺህ 163 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 163 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር የተመለሱት 947 ወንዶች፣ 200 ሴቶች እና 16 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 49 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ73 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

Please follow and like us: