የህፃናትን መብት በማስጠበቅ ረገድ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የተለያዩ ተግባራትን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሠራል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በህፃናት መብት ጥበቃ ላይ በተለየ መልኩ የፖሊሲ አቅጣጫዎች እንዲቀመጡና የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የሚፈፀሙ ጥቃቶች የሚመዘገቡበትና ተገቢ የሆነ ሁሉን አቀፍ አገልግሎት እንዲያገኙ የህፃናት የመረጃ አያያዝ ሰርዓት እንዲዘረጋ እና የቅንጅት ስራዎች እንዲጠናከሩ እየተደረገ ነው።

በአሁን ወቅት በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደለችውን ህፃን ሄቨን በተመለከተ ለደረሰው ዘግናኝ የሆነ ኢሰብአዊ ወንጀል በተመለከተ ሚኒሰትር መስሪያ ቤቱ የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ይህንን አይነት የህፃናት ጥቃት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በፅኑ ያወግዛል። በተፈፀመው ወንጀል ዙሪያ የተሰጠውን ዉሳኔ አስመልክቶ ይግባኝ ለመጠየቅ የሚኬድበት አግባብ ባለመሆኑ ከፍትህ አካላት እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የምንሰራበትና የምንከታተለው ጉዳይ እንደሆነ እንገልፃለን።

Please follow and like us: