402 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 402 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

በዛሬው እለት 315 ወንዶች፣ 75 ሴቶች እና 12 ጨቅላ ህፃናት ወደ ሀገር የተመለሱ ሲሆኑ ከእነዚህም መካከል 8 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ73 ሺህ 400 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

 

Please follow and like us: