የሴቶችና ማህበራዊ ሴክተር የ2016 በጀት አመት አመታዊ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

(ቢሾፍቱ፣ ነሐሴ 17/ 2016 ዓ.ም) የሴቶችና ማህበራዊ ሴክተር አመታዊ ጉባኤውን በቢሾፍቱ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

“ለተፋጠነ ሀገራዊ እድገትና ለዜጎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በቅንጅት እንሰራለን!” በሚል መሪ ቃል ለሁለት ቀናት በሚያካሄደው ጉባኤ ተሳታፊዎች በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በጉባዔውም የሴቶችና ማህበራዊ ሴክተር የ2016 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና 2017 እቅድ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ተመላክቷል።

ሴክተሩ በሚያካሂደው ጉባኤ ላይ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመምከር የቀጣይ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ እና የጋራ አቋም መግለጫ እንደሚያወጣ ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል። በመድረኩ የፌዴራልና የክልል የሴክተር ቢሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ልዩ ልዩ የሴቶችና የወጣት አደረጃጀቶች፣ የአጋር ድርጅት ተወካዮችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተዋል።

 

Please follow and like us: