የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር መ/ቤት የስራ ሀላፊዎችና ሰራተኞች “የኢትዮጽያን ይግዙ” ኢግዚቢሽን ጎበኙ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተዘጋጀውን “የኢትዮጽያን ይግዙ” ኢግዚቢሽን ጎበኙ።

በጉብኝቱ ሀገራዊ የንግድ እንቅስቃሴ ጅምር ከየት ወዴት እንደሆነና በተለያዩ ጊዜያት በመሪነት ተቋሙን የመሩትን የስራ ኃላፊዎች ለመገንዘብ ተችሏል። በኤግዚቢሽኑ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ዋና ዋና ምርቶች የታዩ ሲሆን የተለያዩ የሀገር ውስጥ ምርቶች ግብይት ሂደቱንም መመልከት ተችላል። ሚኒስቴር መ/ቤቱ ስራዎቹን በቋሚነት ለእይታ የሚበቀበት የንግድ ሙዚየም ማዘጋጀቱም ተገልጻል።

 

Please follow and like us: