ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለእንረዳዳ አረጋውያን በጎ አድራጎት ማህበር የ2 መቶ ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከእንረዳዳ የአረጋውያን  በጎ አድራጎት ማህበር ጋር በመተባበር አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለአረጋዊያን ማዕድ አጋርተዋል።

በተጨማሪም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለእንረዳዳ አረጋውያን በጎ አድራጎት ማህበር የ2 መቶ ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል። በመርሃ ግብሩ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተሰፋዬ አረጋውያን ያካበቱትን እውቀት፣ ልምድና ተሞክሮ ለተተኪው ትውልድ በማስተላለፍ እሴቶቻችን እንዲጠበቁ ብልም ለሀገር ልማትና እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያበርከቱ ገልፀዋል፡፡ የሀገር ባለውለታ ለሆኑት አረጋውያን ሁሉም ፍቅርና ክብር ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል።

በዕድሜና በሌሎች ተጓዳኝ ምክንያቶች አረጋውያን ለችግር እንዳይጋለጡ አቅም በፈቀደ መጠን ሀሉም ድጋፍና ክብካቤ እንዲያደርግም መልዕክት አስተላልፈዋል። ለአረጋውያን ያለን ክብርና ፍቅር ለመግለፅና በዓሉን ተደስተው እንዲያሳልፉ ለማስቻል ማዕድ የማጋራት  መርሃ ግብሩ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል። ወደፊትም የተለያዩ አካላትን በማስተባበር ለአረጋውያን የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

 

Please follow and like us: