15ኛውን አለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ ጉባኤ በኢትዮጵያ ለማካሄድና ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ለሚያካሂዳቸው ተጨማሪ ስራዎች ከተለያዩ አጋርና ባለድርሻ አካላት የሀብት ማሰባሰብ ስራዎች ተጠናክረው አንደሚቀጥሉ ተገለጸ፡፡

Yየሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እና የተባበሩት መንግስታት ረዳት ሴክሬተሪ ጀነራል እና በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ ዶ/ር ራሚዝ አልካባሮቭ በኢትዮጵያ ለሚካሄደው 15ኛውን አለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ ጉባኤና ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ለሚያካሂዳቸው ተጨማሪ ስራዎች ሀብት ማሰባሰብ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

15ኛው አለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ ጉባኤ በያዝነው አመት በኢትዮጵያ እንደሚካሄድ ያስታወሱት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ለዚህም ከተለያዩ አጋርና ባለድርሻ አካላት የሀብት ማሰባሰብ ስራዎች ተጠናክረው አንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሯ እንደገለጹት ሚኒስቴሩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማህበር ጋር በመተባበር የዓለም የምልክት ቋንቋ ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ እንደሚካሄድ ገልጸው ጉባኤውን በተሳካ መልኩ ለማካሄድ እስካሁን የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እተካሄዱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለዚህም ዝግጅት ይረዳ ዘንድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች ለጉባዔው መሳካት የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ ጠይቀዋል፡፡

ሚኒስትሯ አክለውም መስሪያቤቱ ለሚያካሂዳቸው ተጨማሪ ስራዎች ለአብነትም ሴት ወጣቶችን በኢኮኖሚ ለማብቃት የሚያግዙ ስራዎችን በጋራ መስራት፣ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን መከላከል እና የስርዓተ ጾታ እኩልነትን ማረጋገጥ ላይ አተኩረው ለሚሰሩ ስራዎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ረዳት ሴክሬተሪ ጀነራል እና በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ ዶ/ር ራሚዝ አልካባሮቭ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በተለይም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህን ትልቅ አለምአቀፍ ጉባኤ ለማዘጋጀት የወሰደውን ተልዕኮ አድንቀው ጉባኤውን በተሳቨቨካ መልኩ ለማካሄድ እንደሚያግዙ ቃል ገብተዋል።

በተጨማሪም ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ለሚያካሂዳቸው ተጨማሪ ስራዎች በተለያ የድጋፍ መስኮች ለመተባበርና ለማገዝ ቃል ገብተዋል፡፡ በጉባዔው ከተለያዩ የአለም አገራትና ተቋማት የተወጣጡ ከ600 በላይ ተሳታፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Please follow and like us: