817 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 817 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

በእለቱ ወደ ሀገር የተመለሱት ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 14 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ እስካሁን ከ83 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

 

Please follow and like us: