የአለም ምግብ ኘሮግራም ከሰብአዊ ድጋፍ ባሻገር የዜጎችን የአኗኗር ዘይቤ በዘላቂነት ለመቀየር የሚሰራውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ ።

ይህ የተገለፀው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) የአለም ምግብ ኘሮግራም በኢትዮጵያ ተወካይ እና ካንትሪ ዳይሬክተር የሆኑትን ዝላታን ሚሊስክን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።

በውይይቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደገለጹት የአለም ምግብ ኘሮግራም ከሰብአዊ ድጋፍ ባሻገር በሌሎች የዜጎችን የአኗኗር ዘይቤና ህይወት በዘላቂነት ለመቀየር በኢትዮጵያ እየሰራ ያለውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠይቀዋል። ሚኒስትሯ እንደገለፁት የአለም ምግብ ኘሮግራም
በማህበራዊ ጥበቃ ፣ የከተማና የገጠር ሴፍቲኔት ፕሮግራሞ፣ በኮቪድ 19 ወቅት ላበረከተው አስተዋፅኦና ለሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርን እስካሁን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ላበረከተው አስተዋፅኦም እውቅና ሰጥተዋል።

በተጨማሪም በቀጣይ በማህበራዊ ጥበቃ፣ በማሕበራዊ ጥበቃ ኮንፍረንስ፣ በሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በተለይም በግብርናው ዘርፍ እንዲሠማሩ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ዘርፎች በትብብር ለመስራት ጠይቀዋል። የአለም ምግብ ኘሮግራም የኢትዮጵያ ተወካይ እና ካንትሪ ዳይሬክተር ዝላታን ሚሊስክን በበኩላቸው ድርጀቱ ለተሰጠዉ እውቅና አመስግነው ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በምግብ ራስን ለመቻል እያደረገች ያለችው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል። በቀጣይም ኘሮግራሙ ከሰብአዊ ድጋፍ ባሻገር የዜጎችን የአኗኗር ዘይቤ በዘላቂነት ለመቀየር የሚያደርገውን ጥረት ለመቀጠል ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ፣ ከሌሎች አጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብርና በቅንጅት ለመስራት ቃል ገብተዋ

Please follow and like us: