ኢትዮጵያ እና ቺሊ በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ዘርፎች ላይ ተወያዩ::

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ዛሬ በፅ/ቤታቸው በኢትዮጵያ የቺሊ አምባሳደር ከሆኑት አምባሳደር ሮድሪጎ ኤድዋርዶ ጉዝማን ባሮስ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደገለፁት ኢትዮጵያ እና ቺሊ እስካሁን የገነቡትን ውጤታማ የእርስ በርስ ግንኘኙኑት ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግ እንደሚገባ ገልፀዋል። ሚኒስትራ አክለውም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለየም በታዳጊ ሴቶች ትምህርት፣ በሴቶች ኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና የሴት ዲፕሎማቶችን ተሳትፎ ማሳደግ ላይ ትኩረት ሰቶ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው በነዚህና በሌሎች የትብብር መስኮች ላይ በጋራ ለመስራት ያላቸውን ተነሳሽነት ጠቅሰዋል።

አምባሳደር ሮድሪጎ ኤድዋርዶ ጉዝማን ባሮስ በበኩላቸው የተለያዩ የትብብርና የቅንጅት መስኮች ላይ ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ጋር ለመስራት እንደሚፈልጉ ገልፀው በቅርቡም ለልምድ ልውውጥ የቺሊ የልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገባ ገልፀዋል።

Please follow and like us: