886 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 886 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር የተመለሱት ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 14 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ እስካሁን ከ84 ሺህ 700 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

 

Please follow and like us: