ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉር ሪጅናል የግሎባል ቻይልድ ማዕከል (Rigonal GlobalChild Hubs) እንድትሆን ተመረጠች።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ የግሎባል ቻይልድ ኮሚቴ ምክትል ሠብሣቢና የፕሮጀክቱ ዳይሬክተር ዶ/ር ዚባ ቫግህሪ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይታቸውም ግሎባል ቻይልድ በህጻናት መብት እየሰራቸው በነበረና ወደፊት በሚሰራቸው ጉዳዮች ዙሪያም በዝርዝር አንስተዋል። ክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በዚሁ ጊዜ፥ ግሎባል ቻይልድ ከካናዳ ውጭ በአምስት አህጉሮች የግሎባል ቻይልድ ማዕከሎችን (Global Child Hubs) ለማቋቋም ሲያስብ በአፍሪካ ኢትዮጵያ የማዕከሉ ዋና መዳረሻ እንድትሆን በመምረጣቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

የግሎባል ፈንድ ዳይሬክተር ዶ/ር ዚባ ቫግህሪ በበኩላቸው፥ ግሎባል ቻይልድ በዋናነት በካናዳ መንግስት የሚደገፍ መሆኑን አንስተው ለበርካታ ዓመታት በህጻናት መብት ላይ ሲሰራ መቆየቱን አውስተዋል። ድርጅቱ በህጻናት መብት ዙሪያ የተለያዩ ጥናቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን ጠቁመው ሪፖርቱን ይፋ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ያነሱ ሲሆን በቀጣይ በአምስት ክፍለ አህጉር ውስጥ አምስት የተለያዩ የግሎባል የህፃናት ማዕከሎችን ለማቋቋም እቅድ እንዳላቸው ገልጸዋል።

ከአፍሪካ የሕፃናት ፖሊሲ ፎረም ጋር ያለውን ጠንካራ እና ቀጣይነት ያለው ትብብር ግምት ውስጥ በማስገባትም ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ግሎባል የህጻናት ማዕከል ሆና እንድታገለግል መመረጧን ገልጸዋል። በቀጣይ በተያዘው እቅድ አተገባበር ዙሪያ ተከታታይና ውጤታማ የሚያደርጉ ውይይቶች እንደሚደረጉም ተገልጿል።

Please follow and like us: