በህልውና ዘመቻው ለተፈናቀሉና በደብረብርሃን ከተማ ለተጠለሉ ወገኖች ድጋፍ ተደረገ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ኤርጎጌ ተስፋዬ በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሚጠበቁ አገልግሎቶች መካከል አንዱ በማህበራዊ አገልግሎቶች ዘርፍ ንቁ ተሳትፎ ማድረግና ለተከሰቱ ሰብዓዊ ቀውሶች ፈጣን ምላሽ መስጠትና ማህበረሰቡን ከችግሩ መታደግ በመሆኑ በዚህ ወቅት ለተፈናቀሉ ወገኖች በፍጥነት በመድረስ አርባምንጭ ዩንቨርሲቲ ይህን ድጋፍ ማድረጉ ለሌሎች የትምህርት ተቋማት አርዓያነት የጎላ ነው ብለዋል፡፡

የአርባምንጭ ዩንቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ዳምጠው ደርዛ በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት በህልውና ዘመቻው ለተፈናቀሉ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ የሁሉም ዜጋ ሃላፊነት መሆኑን ጠቅሰው የተደረገው ድጋፍ አንድ ሚሊየን ብር የሚገመት የተዘጋጀ የጤፍና ሽሮ ዱቄት መሆኑን ገልጰዎል ።ፕሬዘዳንቱ አክለውም ይህ ድጋፍ ሁለተኛው ዙር መሆኑንና በሌሎች አካባቢ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *