በአሰቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን እንዴት መደገፍ ይቻላል

ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች፡-

  • ለችግር የተጋለጡ በአንድ ቤት ውስጥ በጋራ የሚኖሩ እናት፣ አባት፣ ልጆች፣ የስጋ ዝምድና ያላቸው አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኛ የሆኑ
  • በጦርነቱ ህይወታቸውን ያጡ የቤተሰብ ሀላፊዎች ይመሩት በነበረው ቤተሰብ ያሉትን ነዋሪዎች
  • ደጋፊና ረጂ የለሌላቸው ህጻናትና በአሰቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ሚኖሩ ወላጆች እና እናቶች ትኩረት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

 

  • የዚህ ፕሮግራም ትግበራ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ሆኖ አንድ ዲያስፖራ ለአራት ህጻናት የስፖንሰርሽፕ ድጋፍ ያደረጋል፡፡ ድጋፉም ህጻናቶቹ በሚኖሩበት ቀየ ሆነው የሚደረግ ሲሆን የአንድ የቤተሰብ አባል/ህጻን በወር 800 የኢትዮጵያ ብር መነሻ ሆኖ ድጋፍ አድራጊው እንደ አቅሙና ፍላጎቱ ከዚህ የበለጠ ድጋፍ የሚያደርግበት እና የገንዘብ ክፍያዉ አማራጮች አድራጊው በሚመርጠው የግዜ ሰሌዳ የሚከናወን ይሆናል፡፡

 

  • ለፕሮግራሙ ማስፈጸሚያ የስምምነት ሰነድ ተዘጋጅቶ በሶስት አካላት መለትም ድጋፉ በሚሰጥበት ክልል የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ፣በፌደራል ደረጃ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲሁም በስፖንሰርሺፕ አድራጊው መካከል በሚደረግ የውል ስምምነት የሚተገበር ይሆናል፡፡

 

  • ለተጨማሪ መረጃና የግንኑነት አድራሻ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ካዛንቺስ ወረዳ 08

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *