ለችግረ የተጋለጡና ለጎዳና ህይወት የተዳረጉ ህፃናትን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማቀላቀልና ለማዋሀድ በክልሎች መካከል እንዲሁም ከአጋር አካላት ጋር የስምምነት ሰነድ ለመፈራረም ግብአት የማሰባሰብ ሰራ ተከናውኗል

በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ከሚገኙ ህጻናት መካከል በተለያዩ ምክንያቶች ከቤተሰቦቻቸው ወይም ከአሳዳጊዎቻቸው ተነጥለው ኑሯቸውን እና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ህጻናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ ችግሩን ከምንጩ የማድረቅ ስራ በስፋት መስራት ተገቢ እንደሆነ ተገለፀ ።
ለችግሩ የተጋለጡ ህጻናትን የማቀላቀልና ማዋሀድ ተግባር በተጠናከረ ሁኔታ ለማስቀጠል በጎዳናና ከቦታ ቦታ በስደት ላይ የሚገኙ ህጻናት ተገቢው የተሀድሶ ስልጠና፣ የሙያና የንግድ ክህሎት ስልጠና በመስጠት ከቤተሰቦቻቸውና ከህብረተሰቡ ጋር እንዲቀላቀሉ፣ እንዲዋሀዱና እንዲቋቋሙ ለማድረግ የጋራ አሰራር በመንደፍ ለማከናወን አቅዷል
ስራውንም በአግባቡ ለመፈፀም ወጥና ግልፅ የሆነ አሰራርን በመከተል ስራ እንዲሰራ በክልሎች መካከልና አጋር አካላትን የሚያስተሳስር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ በማዘጋጀት በጋራ ለማዳበርና ግብዓት ለማሰባሰብ እንዲያመች መድረኩ ተፈጥሯል ተብሏል ።
የተሳታፊዎችን ስብጥር በተመለከተ የየክልሎች የህጻናት መብትና ጥበቃ ዳየሬክተሮች፣ ቁልፍ ሴክተር መ/ቤቶች፣ አጋር አካላትና ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህጻናት ጥበቃ ስርአት ማጎልበት ዴስክ ሃላፊና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
የቀጣይ አቅጣጫዎችን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት የተሰበሰቡ ግብአቶችን በማካተት የስምምነት ሰነዱን ማጠናቀቅና የየክልል ሴቶችና ማህበራዊ ቢሮ ሃላፊዎች በተገኙበት እንዲፈራረሙ ማድረግ ነው።
Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *