1 ሺህ 27 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

1 ሺህ 27 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
**************
ጥር 3 ቀን 2015 ዓ.ም በሶስት ዙር በተከናወነ በሳኡዲ አረቢያ በችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1,027 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።
በዛሬው እለት ወደ ሀገር ከተመለሱ 1,027 ዜጎች መካከል 942 ወንዶች፣ 61 ሴቶች እና 24 ህፃናትና እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው።
ለተመላሽ ዜጎች በኤርፖርትና በማቆያ ማእከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ከህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 27,722 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡
Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *