የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከክልሎች ጋራ የ2ዐ15 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ውይይት አካሄደ፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከክልሎች ጋራ የ2ዐ15 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ውይይት አካሄደ፡፡
******************
በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሚኒስቴር መ/ቤቱ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደገለፁት የማህበራዊ ጉዳይ እጅግ ሰፊና ውስብስብ ቢሆንም በሚኒስቴር መ/ቤቱና በክልል ቢሮዎች በርካታ ሥራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡ ይሁን እንጁ የተሰሩ ሥራዎችን እንደ አገር በማቀናጀትና ወደ ሪፖርት በመቀየርና በማጠናቀር ማቅረብ ላይ ክፍተት ያለ በመሆኑ ክልሎች ያከናወኑትን የሥራ አፈፃፀም እንዲያቀርቡና ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከሚተገብራቸው የስራ እንቅስቃሴ ጋር በማጣጣም እንደ አገር ያለውን የማህበራዊ ዕቅድ አፈፃፀም መደራጀት አለበት በማለት አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡ በመሆኑም ክልሎች የስራ አፈፃፀም ሪፖርታቸውን እንዲያቀርቡ እድል ተሰጥቷል።
በዚሁ መሠረት የአዲስ አበባ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ፣ የአዲስ አበባ የወጣቶች ቢሮ፣ የሲዳማ ሴ.ማ.ጉ.ቢሮ፣ የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ፤ የኦሮሚያ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ፤ የአማራ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ፤ የአማራ ክልል ወጣቶች ቢሮ ፤የሀረሪ ብሔራዊ መንግስት የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት፤ የጋምቤላ ሕዝብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሴ/ማ/ጉ/ ቢሮ፤ የአፋር ሴ/ማ/ጉ/ቢሮ፤ የደቡብ ቤ/ቤ/ እና ህዝቦች የሰራተኛና ማህበራዊ ገዳይ ቢሮ ሪፖርታቸውን አቅርበዋል።
በመጨረሻም ክብርት ሚኒስትር በክልሎች የቀረበውን ሪፖርት በጋራ ለሚተገበሩት ሥራዎች መጠናከር ጠቃሚ ልምድ ልውውጥ የሚረዳ በመሆኑ አቅራቤዎችን በማመስገን በቀጣይ የሚ/ር መ/ቤቱ የየዘርፉ ስራአስፈፃሚዎችና ክልሎች በጋራ ሊያከናውኗቸው የሚችሉትን ዋና ዋና ጉዳዩች እንዲተገበሩ አቅጣጫ በመስጠት የእለቱ ውሎ ተጠናቋል።
Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *