በብሔራዊ የወጣቶች ፖሊሲ ማሻሻያ ዙሪያ የዉይይት መድረክ ተካሄደ

(ጥር 17 እና 18/2015) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚ/ር በብሔራዊ የወጣቶች ፖሊሲ ማሻሻያ ዙርያ ከፌደራል ሴክተር ተቋማት እንዲህም ከክልሎችና ከተማ አስተዳደር የወጣቶች ዘርፍ ሴክተሮች እና ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ባለሙያዎች ጋር የመከረ ሲሆን በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የወጣቶች ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሙና አህመድ በ1996 ዓ.ም የወጣው ብሔራዊ የወጣቶች ፖሊሲ ለወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዳበረከተ በመግለፅ ነገር ግን የፖሊሲውን አፈፃፀም ፋይዳ በተመለከተ በተካሄድ ሃገር አቀፍ ጥናት መሰረት በአሁን ጊዜ በሀገራችን ካለው የወጣቶች ቁጥር፣ የወጣቶች ፍላጎት እንዲሁም ሃገራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ሁኔታዎች አንፃር የፖሊሲ ማሻሻያ ማድረግ እንደሚያስፈልግ በጥናቱ መመላከቱን ጠቁመው የመድረኩ ተሳታፊዎችም በሚሻሻለው ፖሊሲ መካተት ያለባቸው የወጣቶች ጉዳዮች በተመለከተ ገንቢ ሃሳቦችን እንደሚሰጡ እምነታቸውን ገልፀዋል::
በመድረኩ ዝርዝር ሀሳቦች ከተሳታፊዎች የቀረቡ ሲሆን በሚሻሻለው ብሔራዊ የወጣቶች ፖሊሲ የወጣቶች ስብዕና ግንባታ ጉዳይ፣ የወጣቶች ሥራ ፈጠራ፣ የወጣቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎ ፣ የወጣቶች ማህበራዊ ተጠቃሚነት፣ ሠላምና ደህንነት፣ የወጣቶች ስደት፣ እንዲህም ፖሊሲው አካታች በመሆን የአካል ጉዳተኞች እና የገጠር ወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት በፖሊሲው ዋና ዋና ጉዳዮች ውስጥ መካተት እንዳለባቸው ተጠቁሟል።
በመጨረሻም ለፖሊሲ ማሻሻያው ግብአት የሚሆኑ በርካታ ጠቃሚ ሃሳቦች ከተሳታፊዎች እንደቀረቡ በመግለፅ በፖሊሲ ቀረፃ እና ድህረ ቀረፃ ሂደት የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላትን የሚያሳትፉ የተለያዩ የውይይት መድረኮች እንደሚፈጠሩ የፖሊሲ ዝግጅት ቡድን አባላት ገልፀዋል::
Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *